FREE TENDER | ነፃ ጨረታ
ቀጥሎ የቀረበው ጨረታ ክፍያ የማይጠይቅና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቱት ነፃ ጨረታ ነው ሌሎች ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በዋልያ ቴንደር ደንበኛ አካውንትዎ እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
These tenders are free to view. You don't need to be a walia tender member to view them.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2016 በጀት ዓመት ለሚሰጡ ስልጠናዎች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የባልትና ውጤቶች፤
- ሎት 2 አትክልትና ፍራፍሬ፣
- ሎት 3 የከብትና የበግ ስጋ፣
- ሎት 4 እንቁላል፣
- ሎት 5 ጤፍ፣
- ሎት 6 ማገዶ እንጨት፣
- ሎት 7 ዳቦ፤
- ሎት 8 በርበሬና
- ሎት 9 ኬክና ቆሎ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ድረስ በሚቆይ ውል የሚቀርብ በግልፅ ጨረታ በማወዳደሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 / ሀምሳ ብር / በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን/አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከሰኔ 05/2015 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኔ 05 /2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 20/2015 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ሰኔ 20/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአመራር አካዳሚው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582262360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት