በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴል ስራ ዘርፍ ቀደምት የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሆቴሉ ውስጥ ለምግብ ግብአት የሚሆኑ የበሬ ስጋ፣ የበግ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ እና አሳ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶችን በተጨማሪም የጸረ ተባይ ርጭት አገልግሎት ለማግኘት በግልፅ ጨረታ ከአቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Opens On: Nov 06, 2023
Closes On: Nov 06, 2023
Region: Addis Ababa
Source: አዲስ ዘመን ጥቅምት 15, 2016

የምግብ ግብአትና የፀረ ተባይ ርጭት  የጨረታ ማስታወቂያ 

በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴል ስራ ዘርፍ ቀደምት የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሆቴሉ ውስጥ ለምግብ ግብአት የሚሆኑ የበሬ ስጋ፣ የበግ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ እና አሳ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶችን በተጨማሪም የጸረ ተባይ ርጭት አገልግሎት ለማግኘት በግልፅ ጨረታ ከአቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ መወዳደር የምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ ያለውን መስፈርት በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ 

♦ በዘርፉ የ2015 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 

♦ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፡፡ 

♦ የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬት መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው፡፡ 

♦ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለ “ገነት ሆቴል” በሚል በማሰራት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

♦ ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ 7 (ሰባት) የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ቢሮ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

♦ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች በአንድ ኪሎ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ጨምሮ የሚያቀርቡበትን የአንድ ኪሎ ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በአስረኛው ቀን 8፡ዐዐ ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋይናንስ ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ አስረኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ በቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል። 

♦ ጨረታው ተጫራቾች ተወካዮች ባሉበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 

♦ አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡ ቀድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ/ገነት ሆቴል/ 

ስተጨማሪ መረጃ፡-0939500000/0911250641 

በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት  ገነት ሆቴል አስተዳደር


← Go Back

Advertisement


Put Your Ads Here, Reach More Peoples
& Business
call us +251942125616