አዲስ ዘመን መስከረም 8/2019
Oct 09, 2026
166
Oromia
1000 ETB
100,000.00
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መሰያ ቁጥር 001/CI/2019
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዘመን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጽህፈት መሣሪያዎችን፤ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ኤሌከትሮንክሶች ፣ ፈርኒቸሮች ፣ የመኪና ጎማዎች ፣ የደንብ ልብስ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
1. ተጫራቾች የ2019 የታደሠ እና አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 ን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
2. ለተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ካርድ "TIN card" ያላቸውና ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
4. ለመንግስት መስራቤቶች በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ያላቸው::
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ለሠነዱ የማይመለስ ብር 1000(አንድ ሺህ) ከፍለው በመግዛት የዋጋ ማቅረቢያቸውን ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፕ በተለያዩ በሁለት ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ በስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የl00,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)ብር CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. አሸናፊው ተጫራች ውል ሲፈርም በተፈራረመው ብር መጠን የውል ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ CPO 10% ማሲያዝ አለበት፡፡
8. አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች በእስፔስፍኬሽኑ መሰረት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ እና በተባለው ጊዜ ውስጥ ለማቅረብ ማሸነፉን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 5(አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ በስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ከመስሪያቤቱ ጋር ውል የመፈረም ግዴታ አለበት፡፡
9. አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ ስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የሚገዛውን የዕቃ ብዛት በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይየሚቆይ ሆኖ 16ተኛው የስራ ቀን ወይም 29/1/2019 ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የሚታሸግ ሆኖ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግልጽ የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የማያግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912001254/0911795887
በምሥራቅ ወስጋ ዞን የስቡ ሲሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት