FREE TENDERS | ነፃ ጨረታዎች
ቀጥሎ የቀረቡት ጨረታዎች ክፍያ የማይጠይቁና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቷቸው ነፃ ጨረታዎች ናቸው ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በደንበኛ አካውንትዎ እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05
ድርጅታችን ከጎልደን አፍሪካ የገዛው ፓልም የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ጎልደን አፍሪካ መጋዘን በቀጥታ ወደ አዲስ አባባ እና አዋሽ ሰባት የሚያጓጉዙ ትራንስፖርተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለስድስት ወራት በሚቆይ ውል ማስጫን ይፈልጋል። ስለሆነም በካራ መካፈል የሚፈልጉ ድርጅቶች
- በጨረታ መመሪያው ላይ የተቀመጡትን ግዴታዎች በሙሉ መወጣት የሚችሎ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል::
- ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሽገና የተጫራች ድርጅቶች ማህተም ያረፈበት ኢንቨሎፕ (ፖስታ) አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ::
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ጥቅምት 18 ቀን 2010 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-22-50
Advertisement