የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋልወ

Opens On: Jul 13, 2022
Closes On: Jul 13, 2022
Region: Addis Ababa
Source: አዲስ ዘመን ሰኔ 7, 2014

FREE TENDER | ነፃ ጨረታ

ቀጥሎ የቀረበው ጨረታ ክፍያ የማይጠይቅና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቱት ነፃ ጨረታ ነው ሌሎች ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በዋልያ ቴንደር ደንበኛ አካውንትዎ  እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
These tenders are free to view. You don't need to be a paying member to view them.

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ፋማዳ/ግሥአቡ/036/2014

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ ገጹ (website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሐምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንከ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም. 8፡30 ሰዓት በፋሲሊቲ ማኔጅመንት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  7. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 551 2400 የውስጥ መስመር 237 ወይም 262 እንዲሁም በቀጥታ 011 550 4931 መጠየቅ ይቻላል

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት


← Go Back