በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ፣ የተለያዩ አልባሳት ፣ ሽቶ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ መለዋወጫዎች ፣ ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Opens On: Jul 29, 2022
Closes On: Jul 29, 2022
Region: Amhara
Source: አዲስ ዘመን ሐምሌ 14, 2014

FREE TENDER | ነፃ ጨረታ

ቀጥሎ የቀረበው ጨረታ ክፍያ የማይጠይቅና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቱት ነፃ ጨረታ ነው ሌሎች ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በዋልያ ቴንደር ደንበኛ አካውንትዎ  እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
These tenders are free to view. You don't need to be a walia tender member to view them.

 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 01_2015

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ሽቶ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣መለዋወጫዎች፤ ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

 1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይርባቸዋል።
 2. በተሽከርካሪዎች ጨረታ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ከተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተ/ቁ 1 የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
 3. ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም።
 4. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች እስከ ሀምሌ 21/2014 ዓ.ም ድረስ ለሀራጅ ጨረታ የቀረቡትን ደግሞ እስከ ሀምሌ 22/2014 ዓ.ም 6:00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6:00 ሰዓት የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ።
 5. ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራጮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀምሌ 21/2014  ዓ.ም. ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈለ በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 መግዛት ይችላሉ።
 6. የግልፅ ጨረታ ሀምሌ 22/2014 ዓ.ም ዓ.ም. 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል።
 7. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በባን በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሀምሌ 22/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:45 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 502 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
 8. የሀራጅ ጨረታ ሀምሌ 22/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል።
 9. ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) (5%) የሚጨመር ይሆናል።
 10. ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጭ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል።
 11. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ በአምስት ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
 12. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻለ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ ይቀርባል።
 13. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት እና ለሃራጅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር ከተቋሙ ማስታወቂያ ቦርድ በመመልከት እና

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


በኢትዮጵያ ውስጥ በየእለቱ የሚወጡ ጨረታዎች እንዲደርስዎት የዋልያ ቴንደር አካውንት ይክፈቱ ወይም በ 0942125616 ይደውሉልን በቀላሉ እኛ አካውንት እንሰጥዎታለን
ስለ አገልግሎቱ ክፍያ https://waliatender.com/pricing ይመልከቱ
የሚከፈለውም በባንክ (ሞባይል ባንኪንግ፣ቀጥታ በባንክ ትራንስፈር፣ቴሌብር፣ሲቢኢ ብር ...የመሳሰሉት ፣ አሊያም በአካል ቃሊቲ ቶታል ካፍደም ፕላዛ 4ኛ ፎቅ f425 )
https://waliatender.com


← Go Back

Advertisement


Put Your Ads Here, Reach More Peoples
& Business
call us +251942125616