የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያሰራ ላቀደው የተለያዩ ተቋም የግንባታ እና የጥገና ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Opens On: Nov 23, 2022
Closes On: Nov 23, 2022
Region: Addis Ababa
Source: አዲስ ዘመን ጥቅምት 29, 2015

FREE TENDER | ነፃ ጨረታ

ቀጥሎ የቀረበው ጨረታ ክፍያ የማይጠይቅና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቱት ነፃ ጨረታ ነው ሌሎች ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በዋልያ ቴንደር ደንበኛ አካውንትዎ  እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
These tenders are free to view. You don't need to be a walia tender member to view them.

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር LK/S/C/D/C/W/O/007/2015

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያሰራ ላቀደው የተለያዩ ተቋም የግንባታ እና የጥገና ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የ2015 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተቋራጮች መሆን ይጠበቅባቸዋል ተጫራቾች ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ከላይ በተጠቀሰው በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን ድረስ በመምጣት ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማይመለስ 6oo (ስድስት መቶ) ብር በመክፍል መውሰድ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል: በተጨማሪም በሰም የታሽገውን 6 ፖስታ የፋይናንሽያል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሽግ እና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሽግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል:: ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሀንፃ 6ተኛ ፎቅ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን በ16 (አስራ ስድስተኛው) ቀን እስከ ጠዋት 4፡oo ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ /technical proposal / እና ፋይናንሻል ሰነድ /financial proposal / ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ በዚሁ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ የቅድመ ብቃት/technical proposal / በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት ይከፈታል።

ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል” ውል ያቋረጠ ተወዳድሮ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BD SECURITY) ሎት 2 1 ሎት 3 እና ሎት 4 (200,000 ብር) ሎት 5 (400,000 ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፋይናንስ አስተዳደር ፑል ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ጽ/ቤቱ ባወጣው የግንባታ ጨረታዎች ከአንድ ፕሮጀክት በላይ መሳተፍ አይቻልም፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡትን ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የሥራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ 1 ዋጋ (Rate) ያልተሞላለት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።

8. ከትንሹ ግምት በታች እና የተጋነነ ዋጋ ያስገባ ተቋራጭ ብሬክዳውን (BREAKDOWN) ማስገባት እንደሚገደድ እናሳውቃለን።

9. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በክፍለ ከተማው ዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል።

10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ማሳሰቢያ- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ የሚከፈት ይሆናል።

አድራሻ ፡- ከአያት አደባባይ ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ኢንጆይ ሞል ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 603 ላይ መሆኑን እንገልጻለን።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት


በኢትዮጵያ ውስጥ በየእለቱ የሚወጡ ጨረታዎች እንዲደርስዎት የዋልያ ቴንደር አካውንት ይክፈቱ ወይም በ 0942125616 ይደውሉልን በቀላሉ እኛ አካውንት እንሰጥዎታለን
ስለ አገልግሎቱ ክፍያ https://waliatender.com/pricing ይመልከቱ
ምንም አይነት ጨረታ ማስታወቂያ አያመልጥዎትም!!
የሚከፈለውም በባንክ (ሞባይል ባንኪንግ፣ቀጥታ በባንክ ትራንስፈር፣ቴሌብር፣ሲቢኢ ብር ...የመሳሰሉት ፣ አሊያም በአካል
ቃሊቲ ቶታል ካፍደም ፕላዛ 4ኛ ፎቅ f425 )
https://waliatender.com


← Go Back

Advertisement


Put Your Ads Here, Reach More Peoples
& Business
call us +251942125616