የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር ሲገለገልበት የነበረውን አንድ ላንድ ክሩዘር ያገለገለ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Opens On: Aug 17, 2021 12:08 AM
Closes On: Aug 17, 2021 12:08 AM
Region: Addis Ababa
Source: ሪፖርተር ሐምሌ 21፣ 2013

ያገለገለ ተሸከርካሪ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር ሲገለገልበት የነበረውን አንድ ላንድ ክሩዘር ያገለገለ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

 1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተሸከርካሪው በሚገኝበት አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ከፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ወይም ወረዳ አንድ ፅ/ቤት አጠገብ በድርጅቱ ቅጥር ጊቢ በአካል በመገኘት ዘውትር ከሰኞአርብ ከጠዋቱ 3፡30-10፡00 ድረስ መመልከት ይችላሉ::
 2. ተጫራቾች ከድርጅቱ የተሸከርካሪውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናቶች ድረስ መግዛት ይችላሉ::
 3. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ጠቅላላ ዋጋ ሀያ አምስት በመቶ (25%) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር በሚል አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል::
 4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል::
 5. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የስጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ (ፖስታ/ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
 6. ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው::
 7. አሽናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በሶስት /3/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በአምስት /5/ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው:: ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል::
 8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ማለትም ነሐሴ 11/2013 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 5፡30 ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙብት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
 9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ::
 10. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0921 01 92 98/09 21 02 17 05/011 348 24 63 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ::

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበርውድ ደንበኞቻችን በዚህ ገፅ የሚመለከቷቸው ጥቂት ነፃ ጨረታዎችን ብቻ ነው።

ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በደንበኛ አካውንትዎ  እዚህ ይግቡ

የደንበኛ አካውንት ከሌለዎት  እዚህ ይመዝገቡ


በየእለቱ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚታወጁ የጨረታ ማስታወቂያዎችን

የዋልያ ቴንደር አባል በመሆን በቀላሉ ያገኟቸዋል!!

ለበለጠ መረጃ
ስልክ-0942125616
       - 0919415260

Follow Us

 facebook darkblue 01 - facebook icon small PNG image with transparent background | TOPpng 


← Go Back