የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የቢሮ ጽሕፈት መሣሪያ ስቴሽነሪ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Opens On: Aug 11, 2022
Closes On: Aug 11, 2022
Region: SNNPR
Source: አዲስ ዘመን ሐምሌ 20, 2014

FREE TENDER | ነፃ ጨረታ

ቀጥሎ የቀረበው ጨረታ ክፍያ የማይጠይቅና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቱት ነፃ ጨረታ ነው ሌሎች ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በዋልያ ቴንደር ደንበኛ አካውንትዎ  እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
These tenders are free to view. You don't need to be a walia tender member to view them.

 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የቢሮ ጽሕፈት መሣሪያ ስቴሽነሪ/ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡_

  1. ተጫራቾች ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከመንግሥት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  2. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ብር በመክፈል ደረሰኙን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና አንድ ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና አንድ ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በአንድነት ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ hልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  5. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/ጽ ቤት

ይርጋዓለም
በኢትዮጵያ ውስጥ በየእለቱ የሚወጡ ጨረታዎች እንዲደርስዎት የዋልያ ቴንደር አካውንት ይክፈቱ ወይም በ 0942125616 ይደውሉልን በቀላሉ እኛ አካውንት እንሰጥዎታለን
ስለ አገልግሎቱ ክፍያ https://waliatender.com/pricing ይመልከቱ
ምንም አይነት ጨረታ ማስታወቂያ አያመልጥዎትም!!
የሚከፈለውም በባንክ (ሞባይል ባንኪንግ፣ቀጥታ በባንክ ትራንስፈር፣ቴሌብር፣ሲቢኢ ብር ...የመሳሰሉት ፣ አሊያም በአካል
ቃሊቲ ቶታል ካፍደም ፕላዛ 4ኛ ፎቅ f425 )
https://waliatender.com


← Go Back

Advertisement


Put Your Ads Here, Reach More Peoples
& Business
call us +251942125616