የአብክመ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለአብክመ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Opens On: Oct 25, 2022
Closes On: Oct 25, 2022
Region: Amhara
Source: በኩር መስከረም 30 2015

FREE TENDER | ነፃ ጨረታ

ቀጥሎ የቀረበው ጨረታ ክፍያ የማይጠይቅና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቱት ነፃ ጨረታ ነው ሌሎች ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በዋልያ ቴንደር ደንበኛ አካውንትዎ  እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
These tenders are free to view. You don't need to be a walia tender member to view them.

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ለአብክመ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል።

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው
 3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
 5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለዕቃዎች ግዥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል።
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
 8.  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን እና ሰአት ይከፈታል።
 10.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 11. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 222 0580 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 9644/ 058 220 9646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአብክመ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ


በኢትዮጵያ ውስጥ በየእለቱ የሚወጡ ጨረታዎች እንዲደርስዎት የዋልያ ቴንደር አካውንት ይክፈቱ ወይም በ 0942125616 ይደውሉልን በቀላሉ እኛ አካውንት እንሰጥዎታለን
ስለ አገልግሎቱ ክፍያ https://waliatender.com/pricing ይመልከቱ
ምንም አይነት ጨረታ ማስታወቂያ አያመልጥዎትም!!
የሚከፈለውም በባንክ (ሞባይል ባንኪንግ፣ቀጥታ በባንክ ትራንስፈር፣ቴሌብር፣ሲቢኢ ብር ...የመሳሰሉት ፣ አሊያም በአካል
ቃሊቲ ቶታል ካፍደም ፕላዛ 4ኛ ፎቅ f425 )
https://waliatender.com


← Go Back

Advertisement


Put Your Ads Here, Reach More Peoples
& Business
call us +251942125616